የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ አገልግሎት |
|
እባክዎ
አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው
ያቅርቡ/ይላኩ፡፡
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከተዘጋጀ በኋላ በኤምባሲያችን ወይም ቆንስላ ጽ/ቤታችን ዘንድ ቀርበው
ፈርመው መረከብ ይጠበቅቦታል፡፡
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 አመት የሚያገለግል ይሆናል፡፡ የአገልግሎቱ ዘመኑ ከ1ዓመት በፊት
ያበቃ መታወቂያ ካርድ ከያዙ በፈቃድዎ መታወቂያ ካርዱን እንደመለሱ ይቆጠራል፡፡
-
የአገልግሎት ዘመኑ እስካለበት ድረስ መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት
ይችላሉ፡፡
-
ከ18
ዓመት በታች ልጆች ካልዎት የልደት ማስረጃውን ከሰጠው አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መ/ቤት በኩል አረጋግጠው
በሁለት ኮፒ በማቅረብ በመታወቂያ ካርዱ ላይ አስመዝግበው ከእርሶ ጋር ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት
ይችላሉ፡፡
|
|
የፖስታ አላላክ መመሪያ
-
በፖስታ ቤት አማካኝነት የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያ ፖስታ መጠቀም
የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው
FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL
መሆን ይገባዋል፡፡
-
የላኩት ፖስታ ወደ
ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን
ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡
|
| |
ሀ. በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነው ለመጀመሪያ ግዜ መታወቂያ ካርዱን ለሚጠይቁ |
|
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች |
| |
የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ሁለት ኮፒ |
| |
የቀድሞ
የኢትዮጵያ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ |
| |
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ማቅረብ |
| |
ሶስት
(3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ
ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) |
| |
የአገልግሎት ክፍያ 100ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ |
| |
-
መኒ ኦርደር /Money
Order/ ወይም
-
ካሽየር ቼክ /Cashier
Check/ ወይም
-
ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ
/Certified Bank Check/
|
| |
መጠየቂያ ቅጽ-1 በሁለት ኮፒ መሙላት
(click here to
download) |
| |
|
ለ. በትውልድ ኢትየጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖራቸው ለባለቤታቸው ለሚጠይቁ |
|
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች |
| |
የታደሰ
የውጭ አገር ፓስፖርት ሁለት ኮፒ |
| |
የጋብቻ
የምስክር ወረቀት ከተሰጠበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ሁለት
ኮፒ (ጋብቻው ቢያንስ ለሁለት አመት የፀና መሆን ይኖርበታል) |
| |
ሶስት
(3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ
ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) |
| |
የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የአመልካች ወይም ባለቤት የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ |
| |
የአገልግሎት ክፍያ 100ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ |
| |
|
| |
መጠየቂያ ቅጽ-2 በሁለት ኮፒ መሙላት
(click here to
download) |
| |
|
|
ሐ. መታወቂያ ካርዱ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ለሚጠይቁ |
-
ያለዎት
መታወቂያ ካርድ ማንዋል (ቢጫው) ከሆነ ባሉት ሶስት ገጻች ላይ ታድሶ ሊሠጠዎ ወይም በአካል መቅረብ ሳያስፈልግዎ
Tracking Number ባለው
(FEDEX,
UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL)
መመለሻ ፓስታ ከነቴምብሩ አያይዘውልን ሲልኩልን ታድሶ በአድራሻዎ ሊላክልዎት ይችላል፡፡ እንዲታደስ ያቀረቡት መታወቂያ ካርድ የሚታደስበት ገጽ ከሌለው ግን በአካል
ቀርበው የተዘጋጀልዎትን ተለዋጭ መታወቂያ ካርድ ፈርመው መረከብ ይኖርበታል፡፡
-
ያለዎት
መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪደብል (አዲስ አበባ ከሚገኘው ከዋናው መ/ቤት የሚሰጠው) ከሆነ እዚያው ላይ ማሳደስ
ስለማይቻል የተዘጋጀለዎትን ተለዋጭ መታወቂያ ካርድ በአካል ቀርበው መረከብ ይኖርቦታል፡፡
|
|
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች |
| |
አገልግሎት ዘመኑ ያበቃው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውንና ኮፒውን ማቅርብ |
| |
የታደሰ
የውጭ አገር ፓስፖርት ኮፒ |
| |
ሁለት
(2) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ
ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) |
| |
የአገልግሎት ክፍያ 40ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ |
| |
|
| |
መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
(click here to
download) |
|
|
|
መ. በጠፋ ወይም በተበላሸ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ |
|
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች |
| |
የታደሰ
የውጭ አገር ፓስፖርት ኮፒ |
| |
የቀድሞ
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ (የመታወቂያ ኮፒ ከሌለዎት መቼ እና ከየት እንደወሰዱት የሚገልፅ
ማስታወሻ አያይዘው ይላኩ) |
| |
ሶስት
(3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ
ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) |
| |
የአገልግሎት ክፍያ 60ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ |
| |
|
| |
መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
(click here to
download) |
|
|
|
ሠ. ሲጠቀሙበት የነበረ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለመመለስ ለሚጠይቁ |
|
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች |
| |
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያውን ማቅረብ |
| |
መታወቂያው በፍላጎትዎ የሚመልሱ ለመሆኑ ማስታሻ ጽፈውና ፈርመው ማቅረብ |
| |
መጠየቂያ ቅጽ-4 መሙላት
(click here to
download) |
|
|